አማርኛ
ቋንቋ
የግዢ ቅርጫት 0

መሠረቱ በአፍሪካ ቀንድ

ልዩ
ዓይነት ወርቅ።

በርካታ ሽልማቶችን ያገኘ ጠጅ።
ለማዕድዎ የቀረበ የባህል ጣዕም።

Great Taste 2025 · የ2 ኮከብ ሽልማት አሸናፊ ጠጃችንን ይወቁ

አንድ ጠርሙስ £16.99 ቫትን ጨምሮ

ወርቃማ መለያና ጥቁር ሰማያዊ የአንገት ሽፋን ያለው የTANA ጠጅ ጠርሙስ ንድፍ
TANAጠጅ · ሜስ
በርካታ ሽልማቶችን ያገኘበአነስተኛ መጠን የተመረተጥራትን በጠበቀ እደ ጥበብ የተዘጋጀ

በዩናይትድ ኪንግደም የመጀመሪያው ተሸላሚ የኢትዮጵያ ጠጅ

Great Taste።
በዳኞቹ አንደበት።

የGreat Taste ዳኞች ስለ ጠጃችን ምን እንዳሉ ይመልከቱ።

የዳኞቹ አስተያየቶች በመጀመሪያ በተጻፉበት የእንግሊዝኛ ቋንቋ ቀርበዋል።

GREAT TASTE 2025

የ2 ኮከብ ሽልማት

“A great drink with food, we feel, halfway between a hoppy beer and gentle off-dry wine. We found it delightful.”
የGreat Taste ሽልማቶች • 2025
ተጨማሪ ይመልከቱ

GREAT TASTE 2023

የ1 ኮከብ ሽልማት

“Rounded, balanced, gently sweet, unusual and a very pleasant surprise with flavours that are cleverly combined to produce a really smooth drink”
የGreat Taste ሽልማቶች • 2023
ተጨማሪ ይመልከቱ

ጥበቡ

ጥቂት ወርቅ።
ደስ የሚል ምሽት።

ለስላሳና ሚዛናዊ ጣዕም ያለው ጠጅ፣ በተራቀቀ የማፍላት ሂደትና በሁለቱ ዋና ግብዓቶቹ ባህሪ የተቀረጸ፦ ጥሬ ማርና ጌሾ

  • ከፍተኛ ጥራት ያለው ማር

    የአበባ መዓዛና ለስላሳ የማር ጣዕም።

  • ጌሾ

    የጠጅ ዋነኛ እፅዋታዊ ግብዓት።

  • በቀስታ የፈላ

    ጠርሙስ ውስጥ በእጅ ከመሞላቱ በፊት፣ ከ60 ቀናት በላይ የፈላ።

የሚቀጥለውን ጣዕም ያግኙ

ታሪክ።
በእያንዳንዱ ጠርሙስ።

Concept packaging visual of a TANA honey wine bottle

ያውቁ ኖሯል?ከ2,000 ዓመታት በላይ ግብዓቶቹና የአዘገጃጀት ሂደቱ በአብዛኛው ሳይለወጡ የቆዩት ጠጅ (T’ej፤ «Teyge» ተብሎ ይጠራል) በዓለም ላይ ካሉ እጅግ ጥንታዊ የአልኮል መጠጦች አንዱ ነው።

TANA ORIGINAL

የኢትዮጵያ ጠጅ (750 ሚሊ ሊትር) (T’ej & Mes)

የአበባ መዓዛ፣ መለስ ያለ የማር ጣዕምና ቀለል ያለ የቅመም ጣዕም። ለስላሳና የሚያረካ ጣዕም ያለው TANA የኢትዮጵያንና የኤርትራን የጠጅ ባህል ወደ ማዕድዎ ያመጣል፤ በጥሩ ምግብና በደስ የሚል ወግ መካከል አብሮ ለመጠጣት ተስማሚ ነው።

የግዢ አማራጭ
የግዢ አማራጭ

Delivery frequency: Deliver every month

በእያንዳንዱ የክፍያ ዑደት፣ ለአንድ ጥቅል £16.99።

በተመረጠው እቅድ መሠረት ተደጋጋሚ አቅርቦት። ግዢውን ከማጠናቀቅዎ በፊት የአቅርቦት ድግግሞሹን፣ የክፍያና የስረዛ ውሎችን ያንብቡ።

Delivery frequency: Deliver every 2 months

በእያንዳንዱ የክፍያ ዑደት፣ ለአንድ ጥቅል £16.99።

በተመረጠው እቅድ መሠረት ተደጋጋሚ አቅርቦት። ግዢውን ከማጠናቀቅዎ በፊት የአቅርቦት ድግግሞሹን፣ የክፍያና የስረዛ ውሎችን ያንብቡ።

Delivery frequency: Deliver every 3 months

በእያንዳንዱ የክፍያ ዑደት፣ ለአንድ ጥቅል £16.99።

በተመረጠው እቅድ መሠረት ተደጋጋሚ አቅርቦት። ግዢውን ከማጠናቀቅዎ በፊት የአቅርቦት ድግግሞሹን፣ የክፍያና የስረዛ ውሎችን ያንብቡ።

ግብርን ያካትታል። መደበኛ የዩናይትድ ኪንግደም አቅርቦት፦ ለአንድ ትዕዛዝ £4.99።

የቅድሚያ ትዕዛዝ — የመላኪያ ቀን ወደፊት ይረጋገጣል።

ጠጅ / ሜስ ምንድን ነው?

ጠጅ ከማር የሚዘጋጅ የኢትዮጵያ መጠጥ ነው። ይህ ባህል በኤርትራም አለ፤ እዚያም ሜስ በሚል ስም ይታወቃል። ማር ከውሃ ጋር ይቦካል፤ ጌሾም ልዩ የእፅዋት ጣዕሙን ይሰጠዋል። TANA የዚህ ባህል የእኛ መግለጫ ነው።

እንዴት ቢቀርብ ይሻላል?

ቀዝቅዞ በወይን ጠጅ ብርጭቆ ያቅርቡት። ከሚወዷቸው የኢትዮጵያ ወይም የኤርትራ ምግቦች ጋር ይሞክሩት፣ ወይም ለማዕድዎ አዲስ ጣዕም ይጨምሩበት።

ለምግብ ቤት ወይም ለሱቅ ማዘዝ ይፈልጋሉ?

የንግድ ቡድናችን ስለ ዋጋ፣ ናሙናና የምርት አቅርቦት መረጃ ይሰጥዎታል። ለንግድ ጥያቄዎች ያግኙን.

በኢትዮጵያ የሚገኘው ጣና ሐይቅ የተመለከተበት የናይልና የዓባይ ካርታ
ጣና ሐይቅ · የዓባይ መነሻ11.917° N · 37.267° E

ስሙ። ባህሉ።

ስሙን ከጣና ሐይቅ ወስዷል።
ሥሩ በአፍሪካ ቀንድ ነው።

የዓባይ ወንዝ መነሻ በሆነው ውብ የኢትዮጵያ ጣና ሐይቅ ስም የተሰየመው ጠጃችን፣ የጠጅን ልዩ ባህሪና ባህል ያከብራል።

TANA መሠረቱን በኢትዮጵያና በኤርትራ የጠጅ ባህሎች ላይ ያደረገ ነው። ለሚያውቁት የለመዱትን ባህል ያስታውሳል፤ ለማያውቁት ደግሞ አዲስ ጣዕም ያስተዋውቃል። ዓላማችን ቀላል ነው፤ ይህን ባህል ለበለጠ ሰው ማካፈል።

የመጀመሪያ ጠርሙስዎን ይምረጡ

ምግብ ቤቶች · ችርቻሮ ነጋዴዎች · ጅምላ ነጋዴዎች

ሽልማት ያገኘ ጠጅ።...አዲስ ዕድል

TANAን ለመሸጥ ስለመውሰድ ይጠይቁን

የንግድ ጥያቄዎች

TANAን ለሽያጭ ያቅርቡ

ለደንበኞችዎ ከተለመደው የወይን ጠጅ ዝርዝር የተለየ ነገር ያቅርቡ። የTANA የማርና ለስላሳ የቅመም ጣዕም፣ ጠጅን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚቀምሱ ሰዎች ማራኪ አዲስ ተሞክሮ ይሰጣል። በ2025 የ2 ኮከብ፣ በ2023 ደግሞ የ1 ኮከብ Great Taste ሽልማት አግኝቷል።

የኢትዮጵያና የኤርትራን የጠጅ ባህሎች ለሚያውቁና ለሚወዱ ደንበኞች፣ TANA የለመዱትን ባህል ያስታውሳል፤ ለጣዕም፣ ለሚዛንና ለጥራት ልዩ ትኩረት ይሰጣል።

ለምግብ ቤቶች፣ ለግል ችርቻሮ መደብሮችና ለአከፋፋይ አጋሮች ስድስት ጠርሙስ የያዙ ሳጥኖችን እናቀርባለን። ስለ ንግድ ዋጋ፣ ናሙናዎችና አቅርቦት ያግኙን።

ሁሉም መስኮች መሞላት አለባቸው።

እነዚህን መረጃዎች ለንግድ ጥያቄዎ ምላሽ ለመስጠት እንጠቀማለን። የግላዊነት ፖሊሲ